
ኮሌጃችንን አዲስ ለተቀላቀሉ የክረምት መርሐ-ግብር ተማሪዎች በመማር ማስተማር ሂደትና ተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ላይ ገለጻ ተደረገ።
ወ/ሶ/ግ/ኮ ሀምሌ 18 /2017 ዓ/ም
ለኮሌጃችን አንደኛ ዓመት የክረምት መርሐ-ግብር ተማሪዎች በመማር ማስተማር ሂደትና ተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ላይ ገለጻ ተሰጥቷል።
የኮሌጃችን ተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብር ማስተባበሪያ ኃላፊ መ/ር ሂርቦ ሻንቆ በዚህ ወቅት፣ በትምህርት አሰጣጥ ሂደት፣ 70/30 የሥልጠና ሞዳሊቲ ትግበራ ፣ ተቋማዊ ምዘና ዜዴና ውጤት አሰጣጥ፣ ትምህርቱን ለማጠናቀቅ የሚፈጀውን ጊዜና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኮሌጃችን ተማሪዎች አገልግሎት ዲን መ/ር አዲሴ ደስታ በበኩላቸው ፣ በተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ላይ ገለጻ የሰጡ ሲሆኑ፣ በገለጻውም በተማሪዎች መብት፣ ዲስፕሊንና በተከለከሉ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

